የምርጫ ውጤት ስለማሳወቅ
31/12/2025 12:00 am
31/12/2025 12:00 am
17/11/2025 12:00 am
የ2018ዓ.ም እጩ የቦርድ አባላትን ጥቆማ መቀበልን ይመላከታል፡፡ የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ የዳሪክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ የ2018ዓም እጩ የቦርድ አባላትን ጥቆማ በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በላይ የተቀመጠውን የተመራጭ እጩዎች መጠቆሚያ ቅጽን ፕሪንት በማድረግና ቅጽን በመሙላት በዋናው ቢሮ በተዘጋጀው የጥቆማ መቀበያ ሳጥን እንድታስገቡ እናሳውቃለን፡፡ ለበለጠ ዝርዝር ማብራሪያ መስፈርቱን በሪፖርትር ጋዜጣ በቀን ሰኔ 29/2017ዓም ና በአዲስ ዘመን ሐምሌ 2/2017ዓም ታትሞ ከወጣው ላይ መመልከት ይችላሉ፡፡
የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) እ.ኤ.አ ሰኔ 30/2024 በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከጠቅላላ መድን ዘርፍ ብር 1.15 ቢሊዮን እና ከህይወትና ጤና መድን ዘርፍ 23.1 ሚሊዩን በድምሩ ብር 1.173 ቢሊዮን የአረቦን ገቢ በማስመዝገብና ከታክስ በፊት ብር 211.2 ሚሊዮን ትርፍ በማግኘት የ2016ዓ.ም ዕቅዱን በታላቅ ስኬት ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡ ይህ የተገለፀው ኩባንያው ታህሳስ 5 ቀን 2017ዓ.ም ባካሄደው 17ኛ የባለአክሲዮኖች መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው፡፡ ኩባንያው በበጀት ዓመቱ ያስመዘገበው ጠቅላላ የአረቦን ገቢ በቀዳሚው ዓመት ካስመዘገበው ብር 827.4 ሚሊዩን አረቦን ጋር ሲነፃፀር የብር 346.1 ሚሊዩን ወይንም የ41.8 በመቶ ብልጫ አለው፡፡
ኩባንያው ከ2015 ዓ.ም (2022/23) አጋማሽ ጀምሮ የህይወትና የጤና መድን አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ በአጭር ጊዜ በህይወት ኢንሹራንስ ዘርፉም አመርቂ እድገት ማስመዝገብ ችሏል፡፡ በኢንዱስትሪ ደረጃ በበጀት ዓመቱ በጠቅላላ መድን ዘርፉ ብር 28.3 ቢሊዮን አረቦን የተሰበሰበ ሲሆን፤ የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ብር 1.178 ቢሊዮን የአረቦን ገቢ በማስመዝገብ የገበያ ድርሻውን 4.38 በመቶ ማድረስ ችሏል፡፡
ኩባንያው በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ ብር 421.9 ሚሊዩን የካሣ ክፍያ በመፈፀም አስተማማኝነቱን በተግባር ያረጋገጠ ከመሆኑም በላይ ከመድን ውል ሥራ ያገኘው ውጤት (Underweiting Result) ብር 280.6 ሚሊዮን ነው፡፡ ይህም ከቀደመው ዓመት ጋር ሲነፃጸር የብር 126.8 ሚሊዮን ወይንም የ82.4 በመቶ ብልጫ አለው፡፡
በተጨማሪም ኩባንያው ካሉት ልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት ምንጮች ብር 143.9 ሚሊዮን ገቢ (other income) ከታክስ በፊት ማግኘት የቻለ ሲሆን በአጠቃላይ በጀት ዓመቱ ኩባንያው ብር 211.2 ሚሊዮን ትርፍ አስመዝግቧል፡፡ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃጸር የብር 135.6 ሚሊዮን ወይም የ179.3 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ ግብርና ህጋዊ መጠባበቂያ ተቀንሶ የተገኘው የተጣራ ትርፍም ብር 185.3 ሚሊዮን ሲሆን፤ የአንድ አክሲዮን ያስገኛው አማካይ የትርፍ ድርሻም /Earning Per Share/ 57.6 በመቶ ሆኗል፡፡
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ የኩባንያው አጠቃላይ ሃብት ብር 2.78 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃጸር የብር 705.9 ሚሊዮን ወይም 33.9 በመቶ እድገት አስመዝግቧል፡፡ በቀዳሚው ዓመት የኩባንያው ባለአክስዮኖች ካፒታሉን ወደ 1.2 ቢሊዩን ለማሳደግ ባስተላለፉት ውሳኔ መሠረት ካፒታሉን ከብር 288.1 ሚሊዮን ወደ ብር 402 ሚሊዮን ማድረስ የተቻለ ሲሆን የታቀደውን ግብ ለማሳካት ተግቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ኩባንያው በአሁኑ ወቅት 347 ሠራተኞች የስራ እድል በመፍጠር በመላው ሀገሪቱ ተደራሽነቱን ለማስፋት በከፈታቸው 45 ቅርንጫፎች እና ሶስት አገናኝ ቢሮዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በተጨማሪም የአካታች የፋይናንስ አገልግሎትን መርህ መሠረት በማድረግ የታካፉል ኢንሹራንስ ለደንበኞቹ ለመስጠት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ያገኘ ሲሆን፤ ኩባንያው አገልግሎቱን ለመጀመር በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡
የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)
አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ታህሳስ 20/2016 ዓ.ም ባከናወነው 7ኛ “አስቸኳይ” ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የማህበሩን ካፒታል ለማሳደግ ጉባኤው ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሠረት ነባር ባለአክሲዮኖች የቀደምትነት መብታችሁን በመጠቀም የተደለደለላችሁን አዲስ አክሲዮኖች በአዋጅ ቁጥር 1243/2013 የንግድ ሕግ አንቀጽ 454 እና 455 መሠረት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 11/2016 ዓ.ም ድረስ አዲስ አበባ ለምትገኙ ባለአክሲዮኖች በአንበሳ ኢንሹራንሽ ሕንፃ ዋና መ/ቤት እንዲሁም በተለያዩ ክልሎች እና አስተዳደሮች ለምትገኙ ባለአክሲዮኖች አቅራቢያችሁ በሚገኙት የማህበሩ ቅርንጫፎች ቀርባችሁ የተዘጋጀውን ፎርም በመሙላት የተደለደለልዎትን አዲስ አክሲዮኖች ሙሉ ገንዘብ በዋጋቸው ከፍለው እንዲያጠናቅቁ በአክብሮት እያሳወቅን፤
ባለአክሲዮኖች የተደለደለላቸውን አዲስ አክሲዮኖች ለመግዛት ሲቀርቡ ተራፊ አክሲዮኖች ካሉና ተጨማሪ አክሲዮን ለማግዛት ፈቃደኛ ከሆኑ የሚገዙትን ተጨማሪ የአክሲዮኖች መጠን በሚዘጋጀው ፎርም ላይ በመሙላት እንዲያረጋግጡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)
የዳይሬክተሮች ቦርድ
በኢ.ፌ.ድ.ሪ የንግድ ሕግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 መሠረት የኩባንያውን የመመስረቻ ፅሁፍ እና መተዳደሪያ ደንብ ማዋሀድ በማስፈለጉ የተዘጋጀውን ረቂቅ የተሻሻለ የመመስረቻ ፅሁፍ በኩባንያው ድህረ-ገጽ ላይ የተጫነ መሆኑን እየገለፅን፤ ያላችሁን አስተያየቶች ሆነ ማናቸውንም ግብአቶች በኩባንያው ዋና መስሪያ ቤት የማህበሩ ፀሐፊ ቢሮ በአካል በመቅረብ እንድትሰጡልን ወይም በሚከተለው የኢ-ሜል አድራሻ haileab@anbessainsurance.com ከአስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ በፊት እንዲልኩልን በማክበር እንጠይቃለን፡፡
የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)
የዳይሬክተሮች ቦርድ
09/12/2023 12:00 am
አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ህዳር 29/2011 ዓ.ም ባከናወነው 5ኛ “ድንገተኛ” ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የኩባንያውን ካፒታል ለማሳደግ ጉባኤው ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት የተደለደለላችሁን አክሲዮን ለመግዛት ፈርማችሁ በ5 ዓመት የጊዜ ገደብ ውስጥ ህጋዊ መብታችሁን ያልተጠቀማችሁ ባለአክሲዮኖች፤
ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ህዳር 29/2016 ዓ.ም ጀምሮ በ14 ቀናት ውስጥ አዲስ አበባ ለምትገኙ ባለአክሲዮኖች በአንበሳ ኢንሹራንሽ ሕንፃ ዋና መ/ቤት እንዲሁም በተለያዩ ክልሎች እና አስተዳደሮች ለምትገኙ ባለአክሲዮኖች አቅራቢያችሁ በሚገኙት የኩባንያው ቅርንጫፎች በመቅረብ እንድትከፍሉ በአክብሮት እየጠየቅን፤ በተባለው ጊዜ ውስጥ ካልከፈላችሁ ግን ኩባንያው ተራፊውን አክሲዮኖች በሀራጅ ለመሸጥ የሚገደድ መሆኑን የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ያሳውቃል፡፡
የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)
የዳይሬክተሮች ቦርድ
አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ በ2014 በጀት አመት ከግብር በፊት ያገኘውን ትርፍ አስታወቀ
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ተቋማዊ አስተዳደር መመሪያ ቁጥር SIB/48/2019 እና የዳይሬክተሮች ቦርድ ምልመላና ምርጫ አፈፃፀም መመሪያ” መሠረት የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ ቅዳሜ ጥቅምት 19 ቀን 2015 ዓ.ም መካሄዱ ይታወሳል፡፡
በዚሁ መሠረት በእለቱ በተካሄደው ምርጫ መሠረት የጉባኤው ጽ/ቤት አባል የሆኑ ድምፅ ቆጣሪዎች፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ የምልመላና ምርጫ ኮሚቴ እና የሠነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ጽ/ቤት ተወካይ በተገኙበት፤ በሁሉም ባለአክሲዮኖች የጠቆሙና የተመረጡ 12 እጩዎች እና ተፅእኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች የተጠቆሙና የተመረጡ 6 እጩዎች በአጠቃላይ በ18 እጩዎች መካከል በተካሄደ ምርጫና የድምፅ ቆጠራ በእጩዎቹ ስም ትይዩ የተገለፀውን ድምፅ ያገኙ ሲሆን፣ በተገኘው ውጤትም፡-
በሁሉም ባለአክሲዮኖች የተመረጡት እጩዎች ከአንደኛ እስከ ስድስተኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት እጩዎች እና ተፅእኖ ፈጣሪ ያልሆኑና ተፅእኖ ፈጣሪ ባልሆኑ ባለአክሲዮኖች ብቻ የመረጡት እጩዎች ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱት እጩዎች ባገኙት ከፍተኛ ድምፅ መሠረት ለሚቀጥሉ ሦስት ዓመታት የኩባንያው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ሆነው እንዲሰሩ፣ እንዲሁም በሁለቱም ምድብ በቂ ድምፅ ያላገኙት እጩዎች በየምድባቸው እንደ ቅድመተከተላቸው በተጠባባቂነት እንዲያዙ፤ የዳይሬክተሮች ቦርድ የምመላ እና ምርጫ ኮሚቴ በሙሉ ድምፅ የወሰነ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
| ደረጃ | የእጩዎች ሙሉ ስም | የባለአክስዮኖች የጋራ ድምፅ | ምርመራ |
|---|---|---|---|
| 1ኛ | አቶ አብርሐም ገ/አምላክ ገ/እግዚአብሄር | 7,872,875 | ተመራጭ የቦርድ አባል |
| 2ኛ | አቶ ክፍሉ ታረቀኝ አበራ | 6,341,575 | ተመራጭ የቦርድ አባል |
| 3ኛ | ኤን.ቲ.ኤች. ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ተወካይ አቶ ሚካኤል ታደሰ ካህሳይ) |
5,395,307 | ተመራጭ የቦርድ አባል |
| 4ኛ | አቶ ወ/ገብርኤል ወዳጆ አስገዶም | 5,086,284 | ተመራጭ የቦርድ አባል |
| 5ኛ | አቶ ሃይለ በርሄ ክንፈ | 5,067,974 | ተመራጭ የቦርድ አባል |
| 6ኛ | ወ/ሮ ብርሃን ሃጎስ ወ/ሩፋኤል | 4,985,599 | ተመራጭ የቦርድ አባል |
| በተጠባባቂነት የተያዙ | |||
| 7ኛ | ዶ/ር ተ/ሀይማኖት ሀ/ስላሴ ተክሉ | 4,912,403 | ተጠባባቂ |
| 8ኛ | አቶ ገ/እግዚአብሄር ተስፋይ መርሻ | 4,066,646 | ተጠባባቂ |
| 9ኛ | አቶ በየነ በላይ በርሄ | 3,179,564 | ተጠባባቂ |
| 10ኛ | ዶ/ር ካሳ ሚካኤል ወ/የሱስ | 1,731,855 | ተጠባባቂ |
| 11ኛ | አቶ አረጋኸኝ ሲሳይ ገ/ወልድ | 1,251,375 | ተጠባባቂ |
| 12ኛ | ዶ/ር ገ/አብ ገ/እግዚአብሄር አብርሃ | 380,778 | ተጠባባቂ |
| ደረጃ | የእጩዎች ሙሉ ስም | ተፅእኖ ፈጣሪ ያልሆኑ ባለአክስዮኖች ብቻ ድምፅ | ምርመራ |
|---|---|---|---|
| 1ኛ | አቶ ቶማስ ገ/ማርያም ገ/ተንሳይ | 1,973,927 | ተመራጭ የቦርድ አባል |
| 2ኛ | አቶ ረዘነ ሃይሉ ወ/ገብርሄል | 1,701,232 | ተመራጭ የቦርድ አባል |
| 3ኛ | ዶ/ር ተካ ባራኺ ጎሹ | 1,639,837 | ተመራጭ የቦርድ አባል |
| በተጠባባቂነት የተያዙ | |||
| 4ኛ | አቶ አርአያ ተስፋዬ ገ/ህይወት | 1,010,131 | ተጠባባቂ |
| 5ኛ | አቶ ካህሳይ ኃይሌ ገሰሰው | 936,109 | ተጠባባቂ |
| 6ኛ | አቶ ታመነ አለሙ ገመዳ | 324,448 | ተጠባባቂ |