ለተከበራችሁ የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ባለአክሲዮኖች
በየስማችሁ የተደለደለላችሁን አዲስ አክሲዮን እንድትገዙ የተላለፈ
የጋዜጣ ጥሪ
አንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) ታህሳስ 20/2016 ዓ.ም ባከናወነው 7ኛ “አስቸኳይ” ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የማህበሩን ካፒታል ለማሳደግ ጉባኤው ውሳኔ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡
በዚህም መሠረት ነባር ባለአክሲዮኖች የቀደምትነት መብታችሁን በመጠቀም የተደለደለላችሁን አዲስ አክሲዮኖች በአዋጅ ቁጥር 1243/2013 የንግድ ሕግ አንቀጽ 454 እና 455 መሠረት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 11/2016 ዓ.ም ድረስ አዲስ አበባ ለምትገኙ ባለአክሲዮኖች በአንበሳ ኢንሹራንሽ ሕንፃ ዋና መ/ቤት እንዲሁም በተለያዩ ክልሎች እና አስተዳደሮች ለምትገኙ ባለአክሲዮኖች አቅራቢያችሁ በሚገኙት የማህበሩ ቅርንጫፎች ቀርባችሁ የተዘጋጀውን ፎርም በመሙላት የተደለደለልዎትን አዲስ አክሲዮኖች ሙሉ ገንዘብ በዋጋቸው ከፍለው እንዲያጠናቅቁ በአክብሮት እያሳወቅን፤
ባለአክሲዮኖች የተደለደለላቸውን አዲስ አክሲዮኖች ለመግዛት ሲቀርቡ ተራፊ አክሲዮኖች ካሉና ተጨማሪ አክሲዮን ለማግዛት ፈቃደኛ ከሆኑ የሚገዙትን ተጨማሪ የአክሲዮኖች መጠን በሚዘጋጀው ፎርም ላይ በመሙላት እንዲያረጋግጡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ)
የዳይሬክተሮች ቦርድ