News

ኩባንያው በበጀት ዓመቱ ያስመዘገበው ጠቅላላ የአረቦን ገቢ በቀዳሚው ዓመት ካስመዘገበው ብር 1.17 ቢሊዩን አረቦን ጋር ሲነፃፀር የብር 440 ሚሊዩን ወይንም የ37.2 በመቶ ብልጫ አለው፡፡

ኩባንያው ከ2017ዓ.ም (2024/25) በሰጠው ሰፊ የህይወትና የጤና መድን አገልግሎት የሰበሰበው የአረቦን መጠን ብር 40.9ሚሊየን ሲሆን፣ በዚህ የመድን አገልግሎት ዘርፍ የተገኘው የአረቦን ገቢ በቀዳሚው ዓመት ካስመዘገበው ብር 23.1ሚሊዩን አረቦን ጋር ሲነፃፀር የብር 17.8ሚሊዩን ወይንም የ77 በመቶ ብልጫ አለው፡፡ በኢንዱስትሪ ደረጃ በበጀት ዓመቱ በጠቅላላ መድን ዘርፉ ብር 38.5 ሚሊዮን አረቦን የተሰበሰበ ሲሆን፤ የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ አ.ማ ብር 1.57 ቢሊዮን የአረቦን ገቢ በማስመዝገብ የገበያ ድርሻውን 4.1 በመቶ ማድረስ ችሏል፡፡ 

ኩባንያው በበጀት ዓመቱ አጠቃላይ ብር 635.8 ሚሊዩን የካሣ ክፍያ በመፈፀም አስተማማኝነቱን በተግባር ያረጋገጠ ከመሆኑም በላይ ከመድን ውል ሥራ ያገኘው ውጤት (Underweiting Result) ብር 238.7 ሚሊዮን ነው፡፡

በተጨማሪም ኩባንያው ካሉት ልዩ ልዩ የኢንቨስትመንት ምንጮች (other income) ብር 264 ሚሊዮን ገቢ ማግኘት የቻለ ሲሆን በአጠቃላይ በጀት ዓመቱ ኩባንያው ከታክስ በፊት ብር 387.4 ሚሊዮን ትርፍ ማስመዝገብ ችሏል፡፡ ይህም ካለፈው በጀት ዓመት ጋር ሲነፃጸር የብር 181.3 ሚሊዮን ወይም የ87.9 በመቶ ዕድገት አሳይቷል፡፡ ግብርና ህጋዊ መጠባበቂያ ተቀንሶ የተገኘው የተጣራ ትርፍም ብር 336.6 ሚሊዮን ሲሆን፤ የአንድ አክሲዮን ያስገኛው አማካይ የትርፍ ድርሻም /Earning Per Share/ 67.49 በመቶ ሆኗል፡፡

በተጠናቀቀው በጀት ዓመት መጨረሻ ላይ የኩባንያው አጠቃላይ ሃብት ብር 3.53 ቢሊዮን የደረሰ ሲሆን፤ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃጸር የብር 921.4 ሚሊዮን ወይም 35.2 በመቶ እድገት አስመዝግቧል፡፡

ኩባንያው በአሁኑ ወቅት 359 ሠራተኞች የስራ እድል በመፍጠር በመላው ሀገሪቱ ተደራሽነቱን ለማስፋት በከፈታቸው 48 ቅርንጫፎች እና 3 (ሦስት) አገናኝ ቢሮዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም የአካታች የፋይናንስ አገልግሎትን መርህ መሠረት በማድረግ የታካፉል ኢንሹራንስ ለደንበኞቹ ለመስጠት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፍቃድ ያገኘ ሲሆን፤ እ.ኤ.አ. የ2025/26 በጀት ዓመት በተሟላ ሁኔታ አገልግሎቱን ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡


Lion Insurance Company S.C a prominent composite insurance provider announced the launch of Ethiopia\'s First Digital Meter Taxi Trip basedPersonal Accident Insurance Cover; targeting Meter Taxi transport service providers and their passengers.

Lion Insurance Company S.C having Innovation, Yielding Partnership and Protection as its core values have, managed to come up with new approach of selling Trip based Personal Accident Cover in collaboration with the Little Ride hailing company, known as Little App Ethiopia.

Lion Insurance Share Company and Little Ethiopia have been working tirelessly and collaboratively to redefine the way Personal Accident Insurance cover is being offered to the target market. The insurance cover bundled with Little Ride transport service \"Little App Ethiopia\" which we launch today is the first digital Meter Taxi Trip based Personal Accident Insurance cover in Ethiopia. The successful launching of the product signifies the company\'s commitment to yielding partnership and product differentiation.

The insurance policy provides financial compensation for Death, Disability, cost for medical treatment and ambulance service, as a result of incidents causing accidental personal injury.

The way the cover is provided is a show case about availing meaningful financial protection at an affordable price and with convenience to the Little Ride operators and their passengers. Just a single click on mobile APP, to select insurance at the start of a journey, helps drivers and passengers of the Little Ride (Little App Ethiopia) to enjoy up to Birr1,000,000.00 (One Million Birr) personal Accident Insurance cover, per trip.

We know this is just the beginning and we need to work more to expand it further to create more inclusivity and ensure sustainability.

As there are large number of Meter Taxi (commonly known as Ride) service providers and significant number of service users; the convenience, affordability and accessibility thus created will be quite instrumental in promoting financial inclusion.

Apart\' from promoting financial inclusion, such approaches are also helpful in shaping the market competition through customer segmentation and product differentiation. Participants of the Launching program are provided with the relevant information about the Trip based Personal Accident Insurance Cover including live demonstrations and insights from the development team; about the features that makes it new and truly exceptional.

As we unveil the First Digital Meter Taxi Trip basedPersonal Accident Cover, let us celebrate the spirit of innovation and partnership in pursuit of the endless possibilities that lie ahead.

We believe that the insurance cover we launch today will not only meet but exceed your expectations, because of its value in terms of financial protection, affordability and convenience. we are excited to embark on this journey together.

አንበሳኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ) በባለአክስዮኖች 17ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ የዳራይክተሮች ቦርድ የምርጫና የምልመላ ኮሚቴ አባላትምርጫ ለማድረግ 10 የማህበሩ አባላትን በመጠቆም 05 አባላትን በምርጫ አጽድቋል፡፡

አንበሳ ኢንሹራንስኩባንያቅዳሜ ሚያዚያ 21ቀን 2015ዓ.ም በኢሊሌ ኢንተርናሽናልሆቴል የግማሽ ቀን ልዩ የደንበኞች የምሥጋናና የምክክር ፕሮግራም በማዘጋጀት ዉይይቱምበጥሩ ሁኔታ ተከናውኗል፡፡ በዚህም የጋራ ዉይይትከ60 በላይ ደንበኞች የተሳተፉበት ሲሆን፣ በዉይይት ወቅትም ብዙ ገንቢና በቀጣይን ሊተኮርባቸዉ የሚገባቸዉ ለጥቦችተጠቅሰዋል፡፡

በመጨረሻም ከስብሰባዉ ተሳታፊዎች መካከልም ከባንያዉ አሁን ላለበትደረጃ እንዲደርስ ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽዖ እና የአብሮነት ቆይታ እንዲሁም ወደፊት አብረዉን እንደሚሠሩ በማመን ጭምር የላቀዉጤት ላስመዘገቡ የኩባንያዉ ደንበኞች የምስጋናና የሽልማት ስነ-ሥርዓት ተከናዉኗል፡፡

በወቅቱ የነበሩትን ፕሮግራሞች እና የሽልማት ሂደቶች በከፊል የሚያሳዩምስሎችንም እንደሚከተላዉ ለማሳይት ተሞክሯል፡፡    

የአንበሳ ኢንሹራንስ ኩባንያ (አ.ማ.)የዲሬክተሮች ቦርድ የምልመላና የምርጫ ኮሚቴ ከባለ አክስዮኖች ጥቆማዋችን ሲቀበልና አግባብነት ያላቸውን ማስረጃዎችን ሲያገናዝብ ቆይቷል። በመድን ሰጪዎች የኩባንያ መልካም አስተዳደር መመሪያ ቁጥር SIB/48/2019 አንቀፅ 8(4)(5) በተደነገገው መሰረት ከስር ስማቸው በዝርዝር የተጠቀሱት የተመለመሉ ዕጩዎች ህዳር 13 ቀን 2012  ዓ.ም. በሚካሄደው 12ኛው የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ለዲሬክተሮች ቦርድ አባላት ምርጫ በእጩነት መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን።

  1. አቶ አብርሃ ገብረአምላክ
  2. ዶ/ር መሃሪ ረዳኢ
  3. አቶ ክፍሉ ታረቀኝ
  4. ወ/ሮ ንግስት ገብረመድህን
  5. ወ/ሮ ብርነሽ አባይ
  6. ኤፍ ኤ ቢ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር 
  7. አቶ ቶማስ ገብረማርያም 
  8. አቶ ጸጋይ ብርሃነ
  9. ወ/ሮ ራሄል አለማየሁ
  10. አቶ  ገብረግዚአብሄር ተስፋይ
  11. አቶ ወልደገብርኤል ወዳጆ
  12. አቶ ጥላሁን አምሃ 
  13. አቶ አዋሽ ገብሩ
  14. አቶ ባያብል ፈረደ
  15. ኮሜት ትሬዲንግ ሃላፊነት የተወሰነ የግል ማህበር
  16. አቶ ተክኤ መኩሪያ 
  17. ዶ/ር አስፋወሰን አስራት
  18. አቶ ሃይለስላሴ ይህደጉ

በተጠባባቂነት የተያዙ 

  1. ዶ/ር ተክለሃይማኖት ሃይለስላሴ
  2. አቶ ሞገስ አየለ
  3. አቶ ሃይለስላሴ አማረ
  4. አቶ አረጋኀኝ ሲሳይ

ማሳሰቢያ: ኮሚቴው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ 79ኛ ዓመት ቁጥር 028 መስከረም 28 ቀን 2012 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ እና በሪፖርተር ጋዜጣ በቅፅ 25 ቁጥር 2031 ጥቅምት 5 ቀን 2012 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ ላይ:_

  1. የዕጩ ቦርድ አባላት ዝርዝር በተ/ቁ 3 ላይ አቶ ክፍሉ ታደሰ በማለት የአባት ስም በስህተት የወጣው አቶ  ክፍሉ ታረቀኝ በማለት ያለተካከለ መሆኑን እንዲሁም 
  2. የዲሬክተሮች ቦርድ የሚመረጡበት 12 ኛው  የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባኤ ቀን ከህዳር 06 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ህዳር 13 ቀን 2012 ዓ.ም የተላለፈ መሆኑን በአክብሮት ያሳውቃል

የዲርክተሮች ቦርድ የምልመላና የምርጫ ኮሚቴ